# አጠቃላይ መረጃ እነዚህ ቁጥሮች በመዝሙር 60፡10-12 ካሉት ጥቅሶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው፣ ነገር ግን እንደ 60፡10 ጅማሬ መዝሙር 108:11 “ግን አንተ” የሚል ሐረግ እንደሌለው ልብ በሉ፡፡ # እግዚአብሔር ሆይ፣ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? መዝሙረኛው ልክ እግዚአብሔር እንደ ጣላቸው ለመግለጽ ይህንን ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ “ልክ እንደ ጣልኸን ይመስላል!” ወይም “እግዚአብሔር ሆይ ፣ አንተ የተውኸን ይመስላል!” # ከሠራዊታችን ጋር ወደ ውጊያ አትወጣም መዝሙረኛው፣ እግዚአብሔር የእነርሱን ሠራዊት እንዲረዳ የሚናገረው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ እንዲዋጋ ነው፡፡ “ወደ ጦርነት በሄድን ጊዜ ሠራዊታችንን አላገዝክም” # ከንቱ ነው “ዋጋ ቢስ ነው” # ያሸንፋል “ጠላቶቻችንን ያሸንፋል” # ጠላቶቻችንን ይረግጣል መዝሙረኛው፣ እግዚአብሔር ሠራዊታቸውን እንደሚረዳ ጠላቶቻቸውንም እንደሚያሸንፍ ወደ ታችም እንደሚረግጣቸው ይናገራል፡፡ “ጠላቶቻችንን እንድንረግጥ ይረዳናል” ወይም “ጠላቶቻችንን ማሸነፍ እንድንችል ያደርገናል።