am_tn/psa/045/010.md

24 lines
1.4 KiB
Markdown

# ልጄ ሆይ፣ ስሚ
ንግሥቲቱ ወጣት ሴት በመሆኗ ምክንያት ጸሐፊው “ልጄ” በማለት ሊያነጋግራት ይጀምራል።
# ጆሮሽን አዘንብዪ
ጸሐፊው አንድን ነገር በጥንቃቄ መስማቱን ለመግለጽ በተናጋሪው ሰው አቅጣጫ ጎንበስ ከማለት ጋር ያገናኘዋል። አ.ት፡ “በጥንቃቄ አድምጪ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# የገዛ ሕዝብሽን እርሺ
ንግሥቲቱ ልክ ልትረሳቸው በምትችልበት መልኩ ከእንግዲህ የወገኖቿን እምነትና ልማድ መከተል እንደማይኖርባት ጸሐፊው ይናገራል። አ.ት፡ “ከእንግዲህ የሕዝብሽን ልማድ መከተል አይኖርብሽም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# የአባትሽን ቤት
እዚህ ጋ “ቤት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቤተሰብን ነው። አ.ት፡ “ዘመዶችሽን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# በዚህ መልኩ
“እና” ወይም “እንደዚህ”
# ንጉሡ ውበትሽን ይመኛል
ይህ ንጉሡ ሚስቱ አድርጓት ከንግሥቲቱ ጋር ለመተኛት መፈለጉ በጨዋነት የተነገረበት ነው። (See: Eu- phemism)