am_tn/psa/045/010.md

1.4 KiB

ልጄ ሆይ፣ ስሚ

ንግሥቲቱ ወጣት ሴት በመሆኗ ምክንያት ጸሐፊው “ልጄ” በማለት ሊያነጋግራት ይጀምራል።

ጆሮሽን አዘንብዪ

ጸሐፊው አንድን ነገር በጥንቃቄ መስማቱን ለመግለጽ በተናጋሪው ሰው አቅጣጫ ጎንበስ ከማለት ጋር ያገናኘዋል። አ.ት፡ “በጥንቃቄ አድምጪ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የገዛ ሕዝብሽን እርሺ

ንግሥቲቱ ልክ ልትረሳቸው በምትችልበት መልኩ ከእንግዲህ የወገኖቿን እምነትና ልማድ መከተል እንደማይኖርባት ጸሐፊው ይናገራል። አ.ት፡ “ከእንግዲህ የሕዝብሽን ልማድ መከተል አይኖርብሽም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የአባትሽን ቤት

እዚህ ጋ “ቤት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቤተሰብን ነው። አ.ት፡ “ዘመዶችሽን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በዚህ መልኩ

“እና” ወይም “እንደዚህ”

ንጉሡ ውበትሽን ይመኛል

ይህ ንጉሡ ሚስቱ አድርጓት ከንግሥቲቱ ጋር ለመተኛት መፈለጉ በጨዋነት የተነገረበት ነው። (See: Eu- phemism)