# ልጄ ሆይ፣ ስሚ ንግሥቲቱ ወጣት ሴት በመሆኗ ምክንያት ጸሐፊው “ልጄ” በማለት ሊያነጋግራት ይጀምራል። # ጆሮሽን አዘንብዪ ጸሐፊው አንድን ነገር በጥንቃቄ መስማቱን ለመግለጽ በተናጋሪው ሰው አቅጣጫ ጎንበስ ከማለት ጋር ያገናኘዋል። አ.ት፡ “በጥንቃቄ አድምጪ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # የገዛ ሕዝብሽን እርሺ ንግሥቲቱ ልክ ልትረሳቸው በምትችልበት መልኩ ከእንግዲህ የወገኖቿን እምነትና ልማድ መከተል እንደማይኖርባት ጸሐፊው ይናገራል። አ.ት፡ “ከእንግዲህ የሕዝብሽን ልማድ መከተል አይኖርብሽም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # የአባትሽን ቤት እዚህ ጋ “ቤት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቤተሰብን ነው። አ.ት፡ “ዘመዶችሽን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # በዚህ መልኩ “እና” ወይም “እንደዚህ” # ንጉሡ ውበትሽን ይመኛል ይህ ንጉሡ ሚስቱ አድርጓት ከንግሥቲቱ ጋር ለመተኛት መፈለጉ በጨዋነት የተነገረበት ነው። (See: Eu- phemism)