am_tn/1ch/05/01.md

20 lines
1.2 KiB
Markdown

# የሮቤል
“እንዲሁም” የሚለው ቃል ከትውልዶች ዝርዝር ወደ ወደ ሮቤል ታሪካዊ ዳራ መረጃ ለመሸጋረር እንዲያገለግል የገባ ነው፡፡
# ነገር ግን … ብኵርናው ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ
ይህ በገባሪ ቅርጽ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አት: “ነገር ግን እስራኤል የሮቤልን የብኩርና መብት ለሌላው የእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ሰጡ”
# የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ
ይህ ስለ ሮቤል ከአባቱ ሁለተኛ ሚስት ጋር ስለ መተኛት ለመናገር ለስላሳ መንገድ ነው። መደብ አንድ ወንድና ሚስቱ አብረው የሚኙበት ቦታ ነው፡፡
# ትውልዱ ግን ከብኵርና ጋር አልተቈጠረም
ይህ በገባሪ ቅርፅ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት: “ስለዚህ የቤተሰብ ታሪክ ዝርዝሩ ሮቤልን የበኩር ልጅ አያደርገውም” (ገባሪ እና ተገባሪ፡ ይመልከቱ)
# ሄኖኅ… ፈሉሶ… አስሮን… ከርሚ
እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው፡፡