am_tn/psa/083/001.md

20 lines
1.1 KiB
Markdown

# አጠቃላይ መረጃ፡
ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነግጥም እና ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)
# ዝማሬ፡፡ የአሳፍ ዝማሬ
"ይህ አሳፍ የጻፈው ዝማሬ ነው"
# ጸንቶ/በዝምታ መቆየት
"እኛን ለመርዳት አንዳች አለማድረግ"
# እነሆ፣ ጠላቶችህ ሁከት እየፈጠሩ ነው
እዚህ ስፍራ "ሁከት መፍጠር" ማለት እነርሱ አመጽ እያስነሱ እና በእግዚአብሔር ላይ እያመጹ ነው ማለት ነው፡፡ "እነሆ፣ ጠላቶችህ በአንተ ላይ አምጸዋል"
# አንተን የሚጠሉ ራሳቸውን ቀና እያደረጉ ነው
"እራሳቸውን ቀና እያደረጉ" የሚለው ሀረግ በእግዚአብሔር ላይ እያመጹ ነው የሚለው መገለጫ ነው፡፡ "አንተን የሚጠሉ አንተን እየተቃወሙ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)