# አጠቃላይ መረጃ፡ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነግጥም እና ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ) # ዝማሬ፡፡ የአሳፍ ዝማሬ "ይህ አሳፍ የጻፈው ዝማሬ ነው" # ጸንቶ/በዝምታ መቆየት "እኛን ለመርዳት አንዳች አለማድረግ" # እነሆ፣ ጠላቶችህ ሁከት እየፈጠሩ ነው እዚህ ስፍራ "ሁከት መፍጠር" ማለት እነርሱ አመጽ እያስነሱ እና በእግዚአብሔር ላይ እያመጹ ነው ማለት ነው፡፡ "እነሆ፣ ጠላቶችህ በአንተ ላይ አምጸዋል" # አንተን የሚጠሉ ራሳቸውን ቀና እያደረጉ ነው "እራሳቸውን ቀና እያደረጉ" የሚለው ሀረግ በእግዚአብሔር ላይ እያመጹ ነው የሚለው መገለጫ ነው፡፡ "አንተን የሚጠሉ አንተን እየተቃወሙ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)