am_tn/psa/083/001.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ በዕብራውያን ስነግጥም ውስጥ የተለመደ ነው፡፡ (ስነግጥም እና ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ዝማሬ፡፡ የአሳፍ ዝማሬ

"ይህ አሳፍ የጻፈው ዝማሬ ነው"

ጸንቶ/በዝምታ መቆየት

"እኛን ለመርዳት አንዳች አለማድረግ"

እነሆ፣ ጠላቶችህ ሁከት እየፈጠሩ ነው

እዚህ ስፍራ "ሁከት መፍጠር" ማለት እነርሱ አመጽ እያስነሱ እና በእግዚአብሔር ላይ እያመጹ ነው ማለት ነው፡፡ "እነሆ፣ ጠላቶችህ በአንተ ላይ አምጸዋል"

አንተን የሚጠሉ ራሳቸውን ቀና እያደረጉ ነው

"እራሳቸውን ቀና እያደረጉ" የሚለው ሀረግ በእግዚአብሔር ላይ እያመጹ ነው የሚለው መገለጫ ነው፡፡ "አንተን የሚጠሉ አንተን እየተቃወሙ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)