am_tn/psa/070/001.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ትይዩነት በዕብራይስጥ ግጥም በጣም የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

ለመዘምራን አለቃ

“ይህ በአምልኮ ጥቅም ላይ አንዲውል ለመዘምራን አለቃ ነው”

የዳዊት መዝሙር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) መዝሙሩን የፃፈው ዳዊት ነው ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) የዳዊት አይነት መዝሙር ነው

ለመታሰቢያ

“ይህ መዝሙር የተፃፈው ሰዎች እንዲያስታውሱ ነው”

እነዚያ

“እነዚያ ሰዎች”

ነፍሴን ለመውሰድ

ይህ ፈሊጥ “ሊገድሉኝ” ማለት ነው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ይፈሩ ይዋረዱም

ይህ በገቢር ቅርፅ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “”እግዚአብሔር ያሳፍራቸው፣ በእነርሱም ላይ ውርደት ያምጣባቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ኋላቸው ይመለሱ፣ ይፈሩም

ይህ በገቢር ቅርፅ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ወደ ኋላቸው ይመልሳቸው፣ ስለ ሰሩት ስራ እንዲያፍሩ ይድጋቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ኋላቸው ይመሰሉ

እንዲቆሙ ወይም እንዳይንቀሳቀሱ መደረግ ከጥቃታቸው ወደኋላ እንዲመለሱ እንደማድረግ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲቆሙ ማድረግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንኳ፣ እንኳ የሚሉኝ

ይህ የስላቅ ሳቅ መግለጫ ነው፡፡ “እንኳ እንኳ” የሚለውን በአንተ ቋንቋ በምትጠቀምበት በየትኛውም የሳቅ ድምፅ ልትተካው ትችላለህ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚያ በእኔ ላይ የሚቀልዱና የሚስቁ”