am_tn/psa/070/001.md

40 lines
2.2 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# አጠቃላይ መረጃ፡-
ትይዩነት በዕብራይስጥ ግጥም በጣም የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)
# ለመዘምራን አለቃ
“ይህ በአምልኮ ጥቅም ላይ አንዲውል ለመዘምራን አለቃ ነው”
# የዳዊት መዝሙር
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) መዝሙሩን የፃፈው ዳዊት ነው ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) የዳዊት አይነት መዝሙር ነው
# ለመታሰቢያ
“ይህ መዝሙር የተፃፈው ሰዎች እንዲያስታውሱ ነው”
# እነዚያ
“እነዚያ ሰዎች”
# ነፍሴን ለመውሰድ
ይህ ፈሊጥ “ሊገድሉኝ” ማለት ነው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)
# ይፈሩ ይዋረዱም
ይህ በገቢር ቅርፅ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “”እግዚአብሔር ያሳፍራቸው፣ በእነርሱም ላይ ውርደት ያምጣባቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
# ወደ ኋላቸው ይመለሱ፣ ይፈሩም
ይህ በገቢር ቅርፅ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ወደ ኋላቸው ይመልሳቸው፣ ስለ ሰሩት ስራ እንዲያፍሩ ይድጋቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)
# ወደ ኋላቸው ይመሰሉ
እንዲቆሙ ወይም እንዳይንቀሳቀሱ መደረግ ከጥቃታቸው ወደኋላ እንዲመለሱ እንደማድረግ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲቆሙ ማድረግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
# እንኳ፣ እንኳ የሚሉኝ
ይህ የስላቅ ሳቅ መግለጫ ነው፡፡ “እንኳ እንኳ” የሚለውን በአንተ ቋንቋ በምትጠቀምበት በየትኛውም የሳቅ ድምፅ ልትተካው ትችላለህ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚያ በእኔ ላይ የሚቀልዱና የሚስቁ”