# አጠቃላይ መረጃ፡- ትይዩነት በዕብራይስጥ ግጥም በጣም የተለመደ ነው፡፡ (ግጥም እና ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ) # ለመዘምራን አለቃ “ይህ በአምልኮ ጥቅም ላይ አንዲውል ለመዘምራን አለቃ ነው” # የዳዊት መዝሙር ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) መዝሙሩን የፃፈው ዳዊት ነው ወይም 2) መዝሙሩ ስለ ዳዊት ነው ወይም 3) የዳዊት አይነት መዝሙር ነው # ለመታሰቢያ “ይህ መዝሙር የተፃፈው ሰዎች እንዲያስታውሱ ነው” # እነዚያ “እነዚያ ሰዎች” # ነፍሴን ለመውሰድ ይህ ፈሊጥ “ሊገድሉኝ” ማለት ነው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ) # ይፈሩ ይዋረዱም ይህ በገቢር ቅርፅ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “”እግዚአብሔር ያሳፍራቸው፣ በእነርሱም ላይ ውርደት ያምጣባቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ) # ወደ ኋላቸው ይመለሱ፣ ይፈሩም ይህ በገቢር ቅርፅ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ወደ ኋላቸው ይመልሳቸው፣ ስለ ሰሩት ስራ እንዲያፍሩ ይድጋቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ) # ወደ ኋላቸው ይመሰሉ እንዲቆሙ ወይም እንዳይንቀሳቀሱ መደረግ ከጥቃታቸው ወደኋላ እንዲመለሱ እንደማድረግ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲቆሙ ማድረግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # እንኳ፣ እንኳ የሚሉኝ ይህ የስላቅ ሳቅ መግለጫ ነው፡፡ “እንኳ እንኳ” የሚለውን በአንተ ቋንቋ በምትጠቀምበት በየትኛውም የሳቅ ድምፅ ልትተካው ትችላለህ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚያ በእኔ ላይ የሚቀልዱና የሚስቁ”