am_tn/psa/060/002.md

1.6 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

ዘማሪው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

አንተ ምድሪቱ እንድትናወጥ አደረግህ፤ፍርክስክስም አደረግሀት

ዘማሪው በሀገሩ ውስጥ ያለውን አደጋ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደሆነ እንደዚያ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ስብራትዋን ጠግን

ህዝቡን እንደገና ጠንካራ ማድረግ የመሬትን ወይም የግድግዳን ውስጥ ስብራት መጠገን እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ስብራቶች

የመሬት ወይም የግድግዳ ውስጥ ሰፊ ስንጥቅ

ህዝብህ አስቸጋሪ ነገሮችን እንዲያይ አድርገሀል

እዚህ ላይ “እንዲያይ” የሚለው ቃል “እንዲደርስበት” ወይም “እንዲሰቃይ” የሚለውን ይወክላል፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የሚያንገዳግድ የወይን ጠጅ መጠጣት

ረዳት ማጣት በዙሪያ እንደመንገዳገድ ተደርጎ ተነግሯል፣ እንደምንም ቀጥ ብሎ መቆም እንደመቻል፡፡ “መንገዳገድ” የሚለው ረቂቅ ስምን እንደግስ መግለፅ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንድንገዳገድ የሚያደርግ የወይን ጠጅ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)