24 lines
1.6 KiB
Markdown
24 lines
1.6 KiB
Markdown
|
# አያያዥ ሀሳብ፡-
|
||
|
|
||
|
ዘማሪው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡
|
||
|
|
||
|
# አንተ ምድሪቱ እንድትናወጥ አደረግህ፤ፍርክስክስም አደረግሀት
|
||
|
|
||
|
ዘማሪው በሀገሩ ውስጥ ያለውን አደጋ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደሆነ እንደዚያ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ስብራትዋን ጠግን
|
||
|
|
||
|
ህዝቡን እንደገና ጠንካራ ማድረግ የመሬትን ወይም የግድግዳን ውስጥ ስብራት መጠገን እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ስብራቶች
|
||
|
|
||
|
የመሬት ወይም የግድግዳ ውስጥ ሰፊ ስንጥቅ
|
||
|
|
||
|
# ህዝብህ አስቸጋሪ ነገሮችን እንዲያይ አድርገሀል
|
||
|
|
||
|
እዚህ ላይ “እንዲያይ” የሚለው ቃል “እንዲደርስበት” ወይም “እንዲሰቃይ” የሚለውን ይወክላል፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# የሚያንገዳግድ የወይን ጠጅ መጠጣት
|
||
|
|
||
|
ረዳት ማጣት በዙሪያ እንደመንገዳገድ ተደርጎ ተነግሯል፣ እንደምንም ቀጥ ብሎ መቆም እንደመቻል፡፡ “መንገዳገድ” የሚለው ረቂቅ ስምን እንደግስ መግለፅ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንድንገዳገድ የሚያደርግ የወይን ጠጅ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)
|