# አያያዥ ሀሳብ፡- ዘማሪው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡ # አንተ ምድሪቱ እንድትናወጥ አደረግህ፤ፍርክስክስም አደረግሀት ዘማሪው በሀገሩ ውስጥ ያለውን አደጋ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደሆነ እንደዚያ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # ስብራትዋን ጠግን ህዝቡን እንደገና ጠንካራ ማድረግ የመሬትን ወይም የግድግዳን ውስጥ ስብራት መጠገን እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # ስብራቶች የመሬት ወይም የግድግዳ ውስጥ ሰፊ ስንጥቅ # ህዝብህ አስቸጋሪ ነገሮችን እንዲያይ አድርገሀል እዚህ ላይ “እንዲያይ” የሚለው ቃል “እንዲደርስበት” ወይም “እንዲሰቃይ” የሚለውን ይወክላል፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ) # የሚያንገዳግድ የወይን ጠጅ መጠጣት ረዳት ማጣት በዙሪያ እንደመንገዳገድ ተደርጎ ተነግሯል፣ እንደምንም ቀጥ ብሎ መቆም እንደመቻል፡፡ “መንገዳገድ” የሚለው ረቂቅ ስምን እንደግስ መግለፅ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንድንገዳገድ የሚያደርግ የወይን ጠጅ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)