am_tn/psa/059/012.md

1.6 KiB

ከአፋቸው ስለሚወጣው ኃጢአትና ስለ ከንፈሮቻቸው ቃል

አፍና ከንፈር ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ይወክላል። አ.ት፡ “በሚናገሩት ኃጢአትን ስለሚያደርጉ” ወይም “በሚናገሩት የኃጢአት ንግግር ምክንያት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በትዕቢታቸው ይያዙ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በትዕቢታቸው ምክንያት ሰዎች ይያዟቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ስለሚገልጹት

“ስለሚሉት”

በቁጣ አቃጥላቸው፣ ከእንግዲህ እንዳይገኙ አቃጥላቸው

እነርሱን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እንደ ማቃጠል ወይም መብላት ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ተቆጣቸው፣ አንዳቸውም እንዳይቀሩ አድርገህ አጥፋቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በያዕቆብ

እዚህ ጋ፣ ያዕቆብ የሚያመለክተው እስራኤልን ነው። አ.ት፡ “በእስራኤል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እስከ ምድር ዳርቻ

“በምድር ላይ እጅግ ሩቅ እስከሆነው ቦታ እንኳን”። ይህ በምድር ላይ ሁሉን ስፍራ ይወክላል። አ.ት፡ “በምድር ላይ በሁሉም ቦታ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)