am_tn/psa/059/012.md

24 lines
1.6 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# ከአፋቸው ስለሚወጣው ኃጢአትና ስለ ከንፈሮቻቸው ቃል
አፍና ከንፈር ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ይወክላል። አ.ት፡ “በሚናገሩት ኃጢአትን ስለሚያደርጉ” ወይም “በሚናገሩት የኃጢአት ንግግር ምክንያት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# በትዕቢታቸው ይያዙ
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በትዕቢታቸው ምክንያት ሰዎች ይያዟቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
# ስለሚገልጹት
“ስለሚሉት”
# በቁጣ አቃጥላቸው፣ ከእንግዲህ እንዳይገኙ አቃጥላቸው
እነርሱን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እንደ ማቃጠል ወይም መብላት ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ተቆጣቸው፣ አንዳቸውም እንዳይቀሩ አድርገህ አጥፋቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# በያዕቆብ
እዚህ ጋ፣ ያዕቆብ የሚያመለክተው እስራኤልን ነው። አ.ት፡ “በእስራኤል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
# እስከ ምድር ዳርቻ
“በምድር ላይ እጅግ ሩቅ እስከሆነው ቦታ እንኳን”። ይህ በምድር ላይ ሁሉን ስፍራ ይወክላል። አ.ት፡ “በምድር ላይ በሁሉም ቦታ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)