# ከአፋቸው ስለሚወጣው ኃጢአትና ስለ ከንፈሮቻቸው ቃል አፍና ከንፈር ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ይወክላል። አ.ት፡ “በሚናገሩት ኃጢአትን ስለሚያደርጉ” ወይም “በሚናገሩት የኃጢአት ንግግር ምክንያት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # በትዕቢታቸው ይያዙ ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በትዕቢታቸው ምክንያት ሰዎች ይያዟቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት) # ስለሚገልጹት “ስለሚሉት” # በቁጣ አቃጥላቸው፣ ከእንግዲህ እንዳይገኙ አቃጥላቸው እነርሱን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እንደ ማቃጠል ወይም መብላት ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ተቆጣቸው፣ አንዳቸውም እንዳይቀሩ አድርገህ አጥፋቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # በያዕቆብ እዚህ ጋ፣ ያዕቆብ የሚያመለክተው እስራኤልን ነው። አ.ት፡ “በእስራኤል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # እስከ ምድር ዳርቻ “በምድር ላይ እጅግ ሩቅ እስከሆነው ቦታ እንኳን”። ይህ በምድር ላይ ሁሉን ስፍራ ይወክላል። አ.ት፡ “በምድር ላይ በሁሉም ቦታ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)