am_tn/psa/034/004.md

1.3 KiB

ያህዌን ፈለግሁት

‹‹ፈለግሁት›› የሚለው ዳዊት ያህዌ እንዲረዳው መለመኑን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ ያህዌ ጸለይሁ›› ወይም፣ ‹‹እንዲረዳኝ ያህዌን ለመንሁ››

ወደ እርሱ የሚመለከቱ

‹‹መመልከት›› ከእርሱ ርዳታ መለመንን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዲረዳቸው ወደ እርሱ የሚመለከቱ›› ወይም፣ ‹‹ከእርሱ ብቻ ርዳታ የሚጠብቁ››

ያበራሉ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ደስ ይላቸዋል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ደስ ይላቸዋል››

ፊታቸውም አያፍርም

‹‹ፊታቸው›› ወደ ያህዌ የሚመለከቱ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አያፍሩም›› ወይም፣ ‹‹ይኮራሉ››

ይህ ችግረኛ

ዳዊት ራሱን እንደ ችግረኛ ይቆጥራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተቸግሬ ነበር››

ያህዌ ሰማው

‹‹ሰማኝ›› ያህዌ ረዳኝ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ረዳው››