# ያህዌን ፈለግሁት ‹‹ፈለግሁት›› የሚለው ዳዊት ያህዌ እንዲረዳው መለመኑን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ ያህዌ ጸለይሁ›› ወይም፣ ‹‹እንዲረዳኝ ያህዌን ለመንሁ›› # ወደ እርሱ የሚመለከቱ ‹‹መመልከት›› ከእርሱ ርዳታ መለመንን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዲረዳቸው ወደ እርሱ የሚመለከቱ›› ወይም፣ ‹‹ከእርሱ ብቻ ርዳታ የሚጠብቁ›› # ያበራሉ ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ደስ ይላቸዋል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ደስ ይላቸዋል›› # ፊታቸውም አያፍርም ‹‹ፊታቸው›› ወደ ያህዌ የሚመለከቱ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አያፍሩም›› ወይም፣ ‹‹ይኮራሉ›› # ይህ ችግረኛ ዳዊት ራሱን እንደ ችግረኛ ይቆጥራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተቸግሬ ነበር›› # ያህዌ ሰማው ‹‹ሰማኝ›› ያህዌ ረዳኝ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ረዳው››