am_tn/psa/018/022.md

1.3 KiB

ጻድቅ ሕጐች ሁሉ… ከእነርሱ አልራቅሁም

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ጸሐፊው የደጋገማቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

በፊቴ ነበሩ

‹‹መርተውኛል›› ወይም፣ ‹‹አስታውሻለሁ››

ነቀፋ አልነበረብኝም… ራሴን ከኀጢአት ጠብቄአለሁ

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፡፡ ጸሐፊው የደጋገማቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

በፊቱ ነቀፋ አልነበረብኝም

‹‹በእርሱ ዘንድ ንጹሕ››

ራሴን ከኀጢአት ጠብቄአለሁ

‹‹ኀጢአት አላደረግሁም››

እጆቼ ንጹሕ ነበሩ

‹‹ንጹሕ እጆች›› ምንም በደል አለማድረግ ማለት ነው፡፡ መዝሙር 18፥20 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በደል አልነበረብኝም›› ወይም፣ ‹‹ሥራዬ ትክክል ነበር››

በዐይኖቹ ፊት

ይህ የሚያመለክተው የእግዚአብሔር መገኘት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፊቱ›› ወይም፣ ‹‹በእርሱ ዘንድ››