# ጻድቅ ሕጐች ሁሉ… ከእነርሱ አልራቅሁም ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ጸሐፊው የደጋገማቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ # በፊቴ ነበሩ ‹‹መርተውኛል›› ወይም፣ ‹‹አስታውሻለሁ›› # ነቀፋ አልነበረብኝም… ራሴን ከኀጢአት ጠብቄአለሁ ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፡፡ ጸሐፊው የደጋገማቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ # በፊቱ ነቀፋ አልነበረብኝም ‹‹በእርሱ ዘንድ ንጹሕ›› # ራሴን ከኀጢአት ጠብቄአለሁ ‹‹ኀጢአት አላደረግሁም›› # እጆቼ ንጹሕ ነበሩ ‹‹ንጹሕ እጆች›› ምንም በደል አለማድረግ ማለት ነው፡፡ መዝሙር 18፥20 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በደል አልነበረብኝም›› ወይም፣ ‹‹ሥራዬ ትክክል ነበር›› # በዐይኖቹ ፊት ይህ የሚያመለክተው የእግዚአብሔር መገኘት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፊቱ›› ወይም፣ ‹‹በእርሱ ዘንድ››