am_tn/pro/28/01.md

1.1 KiB

በምድሪቱ በደል ምክንያት

“በደል” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድሪቱ በበደለችው በደል ምክንያት” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የምድሪቱ በደል

ይህ በምድሪቱ የሚኖረው ሕዝብ ኃጢአት ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የምድሪቱ ሕዝብ በደል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ማስተዋልና እውቀት ባለው ሰው

ከዚህ የምናገኘው አመልካች መረጃ ይህ ሰው መሪ ወይም ገዢ መሆነኑ ነው፡፡ “ማስተዋል” እና “እውቀት” የሚሉት ረቂቅ ስሞች እንደ ግስ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሚያስተውልና እንዴት መምራት እንዳለበት በሚያውቅ ሰው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ እና ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)