# በምድሪቱ በደል ምክንያት “በደል” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድሪቱ በበደለችው በደል ምክንያት” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ) # የምድሪቱ በደል ይህ በምድሪቱ የሚኖረው ሕዝብ ኃጢአት ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የምድሪቱ ሕዝብ በደል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ) # ማስተዋልና እውቀት ባለው ሰው ከዚህ የምናገኘው አመልካች መረጃ ይህ ሰው መሪ ወይም ገዢ መሆነኑ ነው፡፡ “ማስተዋል” እና “እውቀት” የሚሉት ረቂቅ ስሞች እንደ ግስ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሚያስተውልና እንዴት መምራት እንዳለበት በሚያውቅ ሰው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ እና ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)