am_tn/pro/08/30.md

1.7 KiB

በአጠገቡ ነበርሁ

አሁንም ጥበብ እየተናገረች ነው፡፡ ጥበብ ከእግዚአብሔር አጠገብ እንደነበረች እየተናገረች ነው፣ ይህን ያለችው እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር የእርሱ ረዳት እንደነበረች ለማመልከት ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዋና ሰራተኛ

ይህ ጠቃሚ ነገሮችን ማለትም የቤት እቃዎችንና ቤቶችን በሚገባ ለመስራት ለአመታት የሰለጠነ ሰው ነው፡፡

ደስ አሰኘው ነበር

“እርሱ እንዲደሰት የማደርገው እኔ ነበርሁ፡፡” “ደስ” የሚለው ቃል እንደ ግስ መገለጽ የሚችል ረቂቅ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእኔ ምክንያት ደስተኛ ነበር” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ዕለት በዕለትዕለት በዕለት

ይህ የልማዳዊ ድርጊት ሃሳብን ወይም ቀጣይነት ያለው ሁኔታን ለመግለጽ የምንጠቀምበት መንገድ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያለማቋረጥ” ወይም “ሁልጊዜ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ በሆነው በመላው ዓለም

“እርሱ የፈጠረው መላው ዓለም” ወይም “እርሱ የፈጠረው በሙሉ”

የሰው ልጆች

ይህ የሚያመለክተው በአጠቃላይ የሰው ልጆችን በሙሉ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ሕልውና ያመጣቸው ሕዝብ በሙሉ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)