# በአጠገቡ ነበርሁ አሁንም ጥበብ እየተናገረች ነው፡፡ ጥበብ ከእግዚአብሔር አጠገብ እንደነበረች እየተናገረች ነው፣ ይህን ያለችው እግዚአብሔር ዓለምን ሲፈጥር የእርሱ ረዳት እንደነበረች ለማመልከት ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # ዋና ሰራተኛ ይህ ጠቃሚ ነገሮችን ማለትም የቤት እቃዎችንና ቤቶችን በሚገባ ለመስራት ለአመታት የሰለጠነ ሰው ነው፡፡ # ደስ አሰኘው ነበር “እርሱ እንዲደሰት የማደርገው እኔ ነበርሁ፡፡” “ደስ” የሚለው ቃል እንደ ግስ መገለጽ የሚችል ረቂቅ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእኔ ምክንያት ደስተኛ ነበር” (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ) # ዕለት በዕለትዕለት በዕለት ይህ የልማዳዊ ድርጊት ሃሳብን ወይም ቀጣይነት ያለው ሁኔታን ለመግለጽ የምንጠቀምበት መንገድ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ያለማቋረጥ” ወይም “ሁልጊዜ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ) # የእርሱ በሆነው በመላው ዓለም “እርሱ የፈጠረው መላው ዓለም” ወይም “እርሱ የፈጠረው በሙሉ” # የሰው ልጆች ይህ የሚያመለክተው በአጠቃላይ የሰው ልጆችን በሙሉ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ሕልውና ያመጣቸው ሕዝብ በሙሉ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)