am_tn/pro/06/14.md

1.1 KiB

ክፋትን ያስባል

“ክፋትን ያቅዳል” ወይም “ክፉ ድርጊቶችን ለመፈጸም ይዘጋጃል”

ሁልጊዜ ጠብን ያነሳሳል

“ሁልጊዜ የጠብ ምክንያት ነው” ወይም “ያለማቋረጥ ግጭትን ይፈልጋል ደግሞም ያባብሳል”

ስለዚህ

“በዚህ ምክንያት”

ጥፋቱ ድንገት ይደርስበታል

ይህ ጥፋቱ እንደ ሰው ወይም እንደ እንስሳ እንደሚያሳድደውና ወዲያውኑ እንደሚደርስበት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥፋቱ ያገኘዋል” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥፋቱ

ይህ በእርሱ ላይ የሚደርስበትን ጥፋት ያሳያል ነገር ግን እርሱ ራሱ የሚያደርሰውንም ጥፋት ያመለክታል፡፡

ድንገት፣ በቅጽበት

ሁለቱም ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ አንዱ ወይም ሁለቱ “ሳይታሰብ” ወይም “በፍጥነት” በሚለው ሊተኩ ይችላሉ፡፡