# ክፋትን ያስባል “ክፋትን ያቅዳል” ወይም “ክፉ ድርጊቶችን ለመፈጸም ይዘጋጃል” # ሁልጊዜ ጠብን ያነሳሳል “ሁልጊዜ የጠብ ምክንያት ነው” ወይም “ያለማቋረጥ ግጭትን ይፈልጋል ደግሞም ያባብሳል” # ስለዚህ “በዚህ ምክንያት” # ጥፋቱ ድንገት ይደርስበታል ይህ ጥፋቱ እንደ ሰው ወይም እንደ እንስሳ እንደሚያሳድደውና ወዲያውኑ እንደሚደርስበት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥፋቱ ያገኘዋል” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # ጥፋቱ ይህ በእርሱ ላይ የሚደርስበትን ጥፋት ያሳያል ነገር ግን እርሱ ራሱ የሚያደርሰውንም ጥፋት ያመለክታል፡፡ # ድንገት፣ በቅጽበት ሁለቱም ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ አንዱ ወይም ሁለቱ “ሳይታሰብ” ወይም “በፍጥነት” በሚለው ሊተኩ ይችላሉ፡፡