am_tn/oba/01/03.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የአብድዩ ራእይ፡አዳምን በተመለከተ ቀጥሏል

የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል

“ልብህ ከስሜት ጋር ተመሳስሏል፡ የኤዶማዊያን ትዕቢት ስለ ጥበቃቸው እንዲታለሉ አድርጓቸዋል፡፡ ተርጓሚው “ትዕቢትህን አታልሎሀል” ወይንም “ትዕቢትህን የማትረታ አድርገህ እንድታስብ አድርጎሃል ”

በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ

“በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ” እዚህ ጋር ሃሳቡ በአለት ስለተከበበ የተጠበቀ ቦታ ነው ፡፡

ከፍ ባለው መኖሪያህ (ማደሪያህ)

“በከፍታ ቦታ ላይ በተሰራው መኖሪያህ ውስጥ”

በልብህ

እዚህ ጋር “በልብህ” ምሳሌያዊ ንግግር ሲሆን “ለራስህ” ተርጓሚው“ለራስህ ትላለህ” ወይም “ታስባለህ”

ወደ ምድር የሚያወርገኝ ማነው?

ይህ ጠያቄ የሚያመለክተው አዳማዊያን ትዕቢተኛና ማነም እንደማይነካቸው ማሰባቸውን ነው፡፡ ተርጓሚው - “ማንም ወደ ምድር ሊያወርዳቸው አይችልም” ወይም “ከየትኛው ሰልፍ እድናለው”

እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን

እነዚህ ሁለት ግነቶች ኤዶም በጣም በከፍታ ቦታ ላይ ቤቱን መስራቱን በማንም በማይደረስ ከፍታ ላይ ብሎ ይናገራል፡፡ ተርጓሚው “ እረግርሀለሁ ክንፍ ኖሮህና ከንስር በላይ ብትበር ቤትህም በኳክብት መካከል ቢሆን”

ከዚያ አወርድሃለው

ትዕቢት ከከፍታ ጋር ሲመሳሰል ትህትና ደግሞ ዝቅ ከማለት ጋር ተመሳስሏል፡፡”ለማውረድ” ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙ አንድን ሰው ትሁት ማድረግ ነው፡፡ ተርጓሚው - ትሁት አደርግሃለው ( ፈሊጣዊ ትርጉም ተመልከት)