am_tn/neh/13/28.md

20 lines
1.3 KiB
Markdown

# ዮአዳ … ኤልያሴብ … ሰንባላጥ
እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)
# ሖሮናዊው
ይህ የሚያመለክተው ከቤት ሖሮን ከተማ የመጣ ሰውን ነው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ)
# እኔም ከአጠገቤ አባረርኩት
“አባረርኩት” ወይም “ኢየሩሳሌምን እንዲለቅቅ አደረግኩት”
# አስባቸው
“ስለ እነርሱ አስብ” ወይም “ያደረጉትን አስታውስ፡፡” እንደዚ አይነት ተመሳሳይ ሐረግ በነህምያ 13፡14 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ
# ክህነትን ስላረከሱ የካህናትንና የሌዋውያንን ቃልኪዳንም ስላፈረሱ
ክህነትን ማርከስ እና ቃልኪዳኑን ማፍረስ ክህነቱንና ቃልኪዳኑን በአካል እንዳረከሱት ተደርጎ ቀርቧል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የክህነቱን ክብር አጉድለዋል፣ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ጋር ያደረግኸውን ቃልኪዳን አፍርሰዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)