am_tn/neh/08/13.md

1.6 KiB

በሁለተኛው ቀን

“በ2ኛው ቀን” ወይም “በሚቀጥለው ቀን” (የመቁጠርያ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ይተረጎምላቸው ዘንድ

“ይተረጎምላቸው” የሚለው ቃል በግስ መልክ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለመረዳት” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በዳስ ይቀመጡ ዘንድ

እነዚህ ሰዎች ከዛፍ ቅርንጫፎችና ከቅጠሎች ይሰሯቸው የነበሩ ጊዜያዊ መጠለያዎች ነበሩ፡፡

ሰባተኛው ወር

“ወር 7፡፡” ይህ የዕብራይስጥ ቀን መቁጠሪያ ሰባተኛ ወር ነው፡፡ በምዕራባውያን አቆጣጠር በመስከረም መጨረሻና በጥቅምት ወር መጀመርያ አካባቢ ያለው ጊዜ ነው፡፡ (ደረጃ የሚያሳዩ ቁጥሮች አና የዕብራይስጥ ወራት የሚለውን ይመልከቱ)

… ብለው ያውጁ ዘንድ

“… ብለው ይናገሩ ዘንድ”

ባርሰነት

ባለ ቀለም አበቦች ያለው ትንሽ የዛፍ ዓይነት፡፡ (የማይታወቁ ነገሮች ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ለምለም ዛፎች

“ብዙ ቅጠል ያላቸው ዛፎች”

እንደተጻፈ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሙሴ ስለዚህ ነገር እንደ ጻፈው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)