# በሁለተኛው ቀን “በ2ኛው ቀን” ወይም “በሚቀጥለው ቀን” (የመቁጠርያ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ) # ይተረጎምላቸው ዘንድ “ይተረጎምላቸው” የሚለው ቃል በግስ መልክ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለመረዳት” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ) # በዳስ ይቀመጡ ዘንድ እነዚህ ሰዎች ከዛፍ ቅርንጫፎችና ከቅጠሎች ይሰሯቸው የነበሩ ጊዜያዊ መጠለያዎች ነበሩ፡፡ # ሰባተኛው ወር “ወር 7፡፡” ይህ የዕብራይስጥ ቀን መቁጠሪያ ሰባተኛ ወር ነው፡፡ በምዕራባውያን አቆጣጠር በመስከረም መጨረሻና በጥቅምት ወር መጀመርያ አካባቢ ያለው ጊዜ ነው፡፡ (ደረጃ የሚያሳዩ ቁጥሮች አና የዕብራይስጥ ወራት የሚለውን ይመልከቱ) # … ብለው ያውጁ ዘንድ “… ብለው ይናገሩ ዘንድ” # ባርሰነት ባለ ቀለም አበቦች ያለው ትንሽ የዛፍ ዓይነት፡፡ (የማይታወቁ ነገሮች ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ) # ለምለም ዛፎች “ብዙ ቅጠል ያላቸው ዛፎች” # እንደተጻፈ ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሙሴ ስለዚህ ነገር እንደ ጻፈው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)