am_tn/mat/10/05.md

2.2 KiB

ማቴዎስ 10፡5-7

ዓያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ለመስበክ ስሄድ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ምን እንደሚያጋጥማቸው መመሪያ መስጠት መጀመሩን እንመለከታለን፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ምንም እንኳ ቁጥር 5 የሚጀምረው ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ላካቸው በማለት ቢሆንም ኢየሱስ ይህንን መመሪያ የሰጣቸው እነርሱን ከመላኩ በፊት ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-events]] ተመልከት) እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን ላካቸው ኤቲ፡ “ኢየሱስ እነዚህ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ላካቸው” ወይም “ኢየሱስ የላካቸው እነዚህን ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ነው” የተላከ ኢየሱስ የላካቸው ለተወሰነ ዓላማ ነው፡፡ “የተላከ” የሚለው ቃል በ MAT 10:2 ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው “አፖስትል” የሚለው ቃል የግሥ ቅርጹ ነው፡፡ አዘዛዘቸው ኤቲ፡ “ምን ማድረግ እንዳለባቸው ነገራው” ወይም “አዘዛቸው” የጠፉት የእስራኤል በጎች ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር አጠቀላይ የእስራኤልን ሕዝብ ከእረኛቸው ከጠፉት በጎች ጋር የሚያነጻጽር ነው፡፡ (UDB) ([[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]] ተመልከት) የእስራኤል ቤት ይህ ገለጻ የእስራኤልን ሕዝብ የሚገልጽ ነው፡፡ ኤቲ፡ “የእስራኤል ሕዝብ” ወይም “የእስራኤል ዘር” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]] ተመልከት) እንዲሁም ስትሄዱ “እናንተ” የሚለው ተውላጠ ስም ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያትን የሚያመለክት ነው፡፡ (: [[rc:///ta/man/translate/figs-pronouns]] ተመልከት) የእግዚአብሔር መንግስ ቀርባለች ይህንን በ MAT 3:2 ውስጥ ያለውን ተመሳሳይ ሀሳብ በተረጎምክበት መንገድ መተርጎም ይኖርብሃል፡፡