am_tn/mat/10/01.md

1.3 KiB

ማቴዎስ 10፡1-1

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርቱን የእርሱን ሥራ ይሠሩ ዘንድ የለከበት ታሪክ መጀመሪያ ነው፡፡ የእርሱ የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን በአንድነት ጠርቶ ኤቲ፡ “የእረሱን ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት ጠርቶ” ሥልጣንን ሰጣቸው በዚህ ክፍል ውስጥ የተሰጣቸው ስልጣን 1) እርሰኩስ መንፈስን ማስወጣት እንዲችሉ 2) በሽታን እና ደዌን ይፈውሱ ዘንድ እንደሆነ ክፍሉ በግልጽ እንደሚናገር እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ማስወጣት ኤቲ፡ “እርኩስ መንፈስ እንዲወጣ ማድረግ” ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች እና ሕመሞች ኤቲ፡ “ሁሉንም በሽታዎች እና ሕመሞች”፡፡ “በሽታ” እና “ሕመም” ተቀራራቢ የሆኑ ነገሮች ይሁን እንዲ ከተቻለ በሁለት የተለያዩ ቃላት ቢተረጎሙ የተሸለ ነው፡፡ “በሽታ” አንድ ሰው እንዲታመም የሚያደርጉት ነገሮች ሲሆኑ፡፡ “በሽታ” ደግሞ በዚህ በሽታ ከመያዛችን የተነሳ የሚሰማን አካላዊ ድካም ወይም ሕመም ነው፡፡