am_tn/mat/03/01.md

2.6 KiB

ማቴዎስ 3፡ 1-3

አጠቃላይ መረጃ፡ ይህ ጸሐፊው የመጥመቁ ዮሐንስን ታሪክ የተነናገረበት አዲስ የታሪኩ አካል መጀመሪያ ነው፡፡ በቁ. 3 ላይ ጸሐፊው የኢየሱስ አገልግሎት መንገድን ያዘጋጅ ዘንድ መጥመቁ ዮሐንስ በእግዚብሔር የተመረጠ መሆኑን ከነብዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ጠቅሶ ጽፏል፡፡ በእነዚህ ቀናት ይህ ዮሴፍ እና የእርሱ ቤተሰብ ከግብጽ ምድር ወደ ናዝሬት ከተመሰሉ ብዙ ዓመታት በኋላ የሆነ ነው፡፡ ይህ ምናልባትም ኢየሱስ አገልግሎቱን ለመጀመር በተቃረበበት ጊዜ የተፈጸመ ነገር ይሆናል፡፡ ኤቲ፡ “ከዚያ በኋላ” ወይም “ከጥቂት ዓመታት በኋላ” ንሰሓ ግቡ ይህ በቅርጹ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ ዮሐንስ ይህንን ለሕዝቡ እየተናገረ ነው፡፡ ([[rc:///ta/man/translate/figs-you]] ተመልከት) የእግዚአብሔር መንግስት ቀርባለች “የእግዚአብሔር መንግስት ቀርባለች” የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር ንጉሥ ሆነ መግዛቱን ያሳያል፡፡ ይህ ሀረግ በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ይገኛል፡፡ ከተቻለ በትርጉምህ ውስጥ “ሰማይ” የሚል ቃልን ተጠቀም፡፡ ኤቲ፡ “በሰማይ የሚኖር አባታችን ራሱን እንደ ንጉሥ አድርጎ በቅርቡ ያሳያል፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-metonymy]] ተመልከት) በነብዩ ኢሳያስ አስቀድሞ ስለ እርሱ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ይህ ስለሆነ ነው ይህ እንዲህ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡፡ “ነብዩ ኢሳያስ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-activepassive]] ተመልከት) የአንድ ሰው ድምፅ በዚህ ሥፍራ ላይ “ድምፅ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሉ ሰውን ነው፡፡ ኤቲ፡ “አንድ ሰው አለ፡፡” ([[rc:///ta/man/translate/figs-synecdoche]] ተመልከት) የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ መንገዱንም አቅኑ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ መንገዱንም አቅኑ”፡፡ ይህ በዮሐንስ ሰዎችን ለኢየሱስ መምጣት ሰዎችን በንሰሓ የሚያዘጋጅ ምሳሌያዊ መልዕክት ነው፡፡ (rc://*/ta/man/translate/figs-metaphor ተመልከት)