am_tn/lam/04/07.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

አለቆችዋ ከበረዶ ይልቅ ጥሩ፥ ከወተት ይልቅ ነጭ ነበሩ

ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1የእየሩሳሌም መሪዎች ጤነኛ ስለነበሩ ለመመልከት እራሱ የሚያምሩ ነበሩ ወይንም 2መሪዎችዋ በህሊናቸው እንደ በረዶ ንፁህ እና እንደ ወተት የነጡ ናቸው።

አለቆችዋ

“የእየሩሳሌም መሪዎች”

ገላቸው ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ቀይ ነበረ

“ሰውነታቸው ከቀይ ዕንቍ የቀላ” ይሄ ጤንነታቸውን ያመለክታል። “ሰውነታቸው ጤነኛ እና ቀይ ነበረ”

ከቀይ ዕንቍ

ጠንካራ ቀይ ከባህር የሚገኝ ለማስጌጥ የሚጠቅም ድንጋይ

ሰንፔር

ውድ ሰማያዊ ቀለም ያለው የከበረ ድንጋይ ለማጌጫነት የሚውል።

ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል

ይሄ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት ፡ 1የመሪዎቻቸውን ቆዳ ፀሓይ አጥቁሮታል ወይንም 2እየሩሳሌም ስትቃጠል የነካቸው ጭስ ፊታቸውን አጥቁሯቸዋል።

በመንገድም አልታወቁም

በቀጥታ መልኩ ፡ “ማንም አይቶ ሊለያቸው አልቻለም” ሊባል ይችላል።

ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል

ከቆዳቸው ሥር ጮማም ሆነ ጡንቻ እንዳልነበረ ያሳያል።

ደርቆአል፤ እንደ እንጨት ሆኖአል

የደረቀው ቆዳቸው ከእንጨት ጋር ተመስሏል