am_tn/isa/51/12.md

20 lines
1.3 KiB
Markdown

# አጠቃላይ መረጃ
ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል
# እኔ፣ እኔ፣ እርሱ ነኝ
‹‹እኔ›› የሚለው የተደገመው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ በቋንቋህ ይህ ያልተለመደ ከሆነ ድግግሙን መተው ትችላለህ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ እርሱ ነኝ››
# እንደ ሣር የሆኑ ሰዎችን… ለምን ትፈራለህ?
ጥያቄው የቀረበው የጌታ ጥበቃ ያላቸው ሰዎችን መፍራት እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህን ዐረፍተ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ሣር የሆኑትን ሰዎች… አትፍራ››
# እንደ ሣር የሆነውን
የሰው ሕይወት አጭር መሆኑንና ቶሎ እንደሚሞት አጽንዖት ለመስጠት ሰዎችን ከሣር ጋር ይመሳስላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ሣር ኖረው በፍጥነት የሚሞቱትን›› ወይም ‹‹እንደ ሣር ጠውልገው ቶሎ የሚጠፉትን››
# እንደ… የሆኑትን
ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ… የሆኑ››