am_tn/isa/51/12.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል

እኔ፣ እኔ፣ እርሱ ነኝ

‹‹እኔ›› የሚለው የተደገመው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ በቋንቋህ ይህ ያልተለመደ ከሆነ ድግግሙን መተው ትችላለህ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ እርሱ ነኝ››

እንደ ሣር የሆኑ ሰዎችን… ለምን ትፈራለህ?

ጥያቄው የቀረበው የጌታ ጥበቃ ያላቸው ሰዎችን መፍራት እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህን ዐረፍተ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ሣር የሆኑትን ሰዎች… አትፍራ››

እንደ ሣር የሆነውን

የሰው ሕይወት አጭር መሆኑንና ቶሎ እንደሚሞት አጽንዖት ለመስጠት ሰዎችን ከሣር ጋር ይመሳስላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ሣር ኖረው በፍጥነት የሚሞቱትን›› ወይም ‹‹እንደ ሣር ጠውልገው ቶሎ የሚጠፉትን››

እንደ… የሆኑትን

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ… የሆኑ››