# አጠቃላይ መረጃ ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል # እኔ፣ እኔ፣ እርሱ ነኝ ‹‹እኔ›› የሚለው የተደገመው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ በቋንቋህ ይህ ያልተለመደ ከሆነ ድግግሙን መተው ትችላለህ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ እርሱ ነኝ›› # እንደ ሣር የሆኑ ሰዎችን… ለምን ትፈራለህ? ጥያቄው የቀረበው የጌታ ጥበቃ ያላቸው ሰዎችን መፍራት እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህን ዐረፍተ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ሣር የሆኑትን ሰዎች… አትፍራ›› # እንደ ሣር የሆነውን የሰው ሕይወት አጭር መሆኑንና ቶሎ እንደሚሞት አጽንዖት ለመስጠት ሰዎችን ከሣር ጋር ይመሳስላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ሣር ኖረው በፍጥነት የሚሞቱትን›› ወይም ‹‹እንደ ሣር ጠውልገው ቶሎ የሚጠፉትን›› # እንደ… የሆኑትን ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ… የሆኑ››