am_tn/isa/48/09.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ስለ ስሜ ስል ቁጣዬን አዘገያለሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ስም›› የያህዌን ማንነት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ማንነቴ ስል ቁጣዬን አዘገያለሁ››

ስለ ክብሬ ስል እናንተን ከማጥፋት እታቀባለሁ

ይህ የዐረፍተ ነገሩ ክፍል ከመጀመሪያው ክፍል ጋር በመሠረቱ ተመሳሳይ ነው፡፡

እነሆ፣ እንደ ብር ባይሆንም፣ አንጥሬሃለሁ፤ በመከራ እቶን አንጽቼሃለሁ

እነርሱ የከበሩ ማዕድኖች የሆኑ ይመስል እቶን ደግሞ እነርሱን የሚያነጻ እሳት ይመስል ያህዌ ሕዝቡን በመከራ ውስጥ እንደሚያነጻ ይናገራል፡፡

ስሜን ለውርደት እንዴት አሳልፌ እሰጣለሁ?

ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው ስሙን ለውርደት አሳልፎ እንደማይሰጥ አጠንክሮ ለማመልከት ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንም ስሜን እንዲያዋርድ አልፈቅድም››