am_tn/isa/48/09.md

20 lines
1.3 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# አጠቃላይ መረጃ
ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡
# ስለ ስሜ ስል ቁጣዬን አዘገያለሁ
እዚህ ላይ፣ ‹‹ስም›› የያህዌን ማንነት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ማንነቴ ስል ቁጣዬን አዘገያለሁ››
# ስለ ክብሬ ስል እናንተን ከማጥፋት እታቀባለሁ
ይህ የዐረፍተ ነገሩ ክፍል ከመጀመሪያው ክፍል ጋር በመሠረቱ ተመሳሳይ ነው፡፡
# እነሆ፣ እንደ ብር ባይሆንም፣ አንጥሬሃለሁ፤ በመከራ እቶን አንጽቼሃለሁ
እነርሱ የከበሩ ማዕድኖች የሆኑ ይመስል እቶን ደግሞ እነርሱን የሚያነጻ እሳት ይመስል ያህዌ ሕዝቡን በመከራ ውስጥ እንደሚያነጻ ይናገራል፡፡
# ስሜን ለውርደት እንዴት አሳልፌ እሰጣለሁ?
ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው ስሙን ለውርደት አሳልፎ እንደማይሰጥ አጠንክሮ ለማመልከት ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንም ስሜን እንዲያዋርድ አልፈቅድም››