am_tn/isa/29/15.md

16 lines
1.5 KiB
Markdown

# አጠቃላይ መረጃ
ኢሳይያስ እየተናገረ ነው ወይም የ29፡13-14 የእግዚአብሔር ንግግር ቀጥሏል
# እቅዳቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ
ሕዝቡ እግዚአብሔር ስለ እቅዱ ሳያውቅ ለማቀድ መሞከራቸው እግዚአብሔር ሊያይ በማይችልበት በጥልቅ ስፍራ እቅዳቸውን ለመሰውር እንደፈለጉ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "እቅዳቸውን ከእግዚአብሔር ለመሰወር የሚጥሩ' ወይም "ለማድረግ ያቀዱትን እግዚአብሔር እንዳይደርስበት ለመከልከል የሚጥሩ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
# ሥራቸው በጨለማ የሆነ
በምስጢር ክፉ ነገሮችን እንደሚያደርጉ ተመላክቷል፡፡ አት፡- "ማንም ሊያያቸው እንዳይችል ክፉ ነገሮችን በጨለማ ውስጥ የሚያደርጉ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
# ማን ያየናል? ማንስ ያውቀናል የሚሉ?
የሚያደርጉትን ማንም እንደማያውቅ ማመናቸውን አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማሉ፡፡ አት፡- "የምናደርገውን ማንም እግዚአብሔርም እንኳን አያየንም ወይም አያውቅም!' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)