am_tn/isa/29/15.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ እየተናገረ ነው ወይም የ29፡13-14 የእግዚአብሔር ንግግር ቀጥሏል

እቅዳቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ

ሕዝቡ እግዚአብሔር ስለ እቅዱ ሳያውቅ ለማቀድ መሞከራቸው እግዚአብሔር ሊያይ በማይችልበት በጥልቅ ስፍራ እቅዳቸውን ለመሰውር እንደፈለጉ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "እቅዳቸውን ከእግዚአብሔር ለመሰወር የሚጥሩ' ወይም "ለማድረግ ያቀዱትን እግዚአብሔር እንዳይደርስበት ለመከልከል የሚጥሩ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ሥራቸው በጨለማ የሆነ

በምስጢር ክፉ ነገሮችን እንደሚያደርጉ ተመላክቷል፡፡ አት፡- "ማንም ሊያያቸው እንዳይችል ክፉ ነገሮችን በጨለማ ውስጥ የሚያደርጉ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ማን ያየናል? ማንስ ያውቀናል የሚሉ?

የሚያደርጉትን ማንም እንደማያውቅ ማመናቸውን አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማሉ፡፡ አት፡- "የምናደርገውን ማንም እግዚአብሔርም እንኳን አያየንም ወይም አያውቅም!' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)