# አጠቃላይ መረጃ ኢሳይያስ እየተናገረ ነው ወይም የ29፡13-14 የእግዚአብሔር ንግግር ቀጥሏል # እቅዳቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ ሕዝቡ እግዚአብሔር ስለ እቅዱ ሳያውቅ ለማቀድ መሞከራቸው እግዚአብሔር ሊያይ በማይችልበት በጥልቅ ስፍራ እቅዳቸውን ለመሰውር እንደፈለጉ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "እቅዳቸውን ከእግዚአብሔር ለመሰወር የሚጥሩ' ወይም "ለማድረግ ያቀዱትን እግዚአብሔር እንዳይደርስበት ለመከልከል የሚጥሩ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት) # ሥራቸው በጨለማ የሆነ በምስጢር ክፉ ነገሮችን እንደሚያደርጉ ተመላክቷል፡፡ አት፡- "ማንም ሊያያቸው እንዳይችል ክፉ ነገሮችን በጨለማ ውስጥ የሚያደርጉ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት) # ማን ያየናል? ማንስ ያውቀናል የሚሉ? የሚያደርጉትን ማንም እንደማያውቅ ማመናቸውን አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማሉ፡፡ አት፡- "የምናደርገውን ማንም እግዚአብሔርም እንኳን አያየንም ወይም አያውቅም!' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)