am_tn/isa/08/08.md

20 lines
1.6 KiB
Markdown

# አጠቃላይ መረጃ
ጌታ የአሦር ሰራዊት እንደ ወንዝ እየጐረፈ ወደ ይሁዳ እንደሚመጣ መናገሩን ቀጥሏል፡፡
# ወንዙ እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል
የአሦር ሰራዊት እንደ ውሃ ጐርፍ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከፍ እያለ ሄዶ እስከ ዐንገታችሁ እንደሚደርስ ወንዝ እጅግ ብዙ ወታደሮች ይመጣሉ››
# ወንዙ
ይህ የሚያመለክተው በአሦር ያለውን የኤፍራጥስ ወንዝ ነው፡፡ ከቤታቸው ተነሥተው በኤፍራጥስ ወንዝ በኩል የሚመጡት የአሦር ወታደሮችም ምሳሌ ነው፡፡ (ኢሳይያስ 8፥7)
# የተዘረጉ ክንፎቹ ይሞላሉ
ይህም ማለት፣ 1) በምሳሌው እንዳየነው፣ ‹‹ወንዝ›› ወደ ደረቁ ምድር ‹‹ይወርዳል፣ ‹‹በክንፎቹም›› ይሸፍናል፡፡ ወይም 2) አሁን ኢሳይያስ ምሳሌውን በመለወጥ ያህዌ ምድሩን እንደሚጋርድ ወፍ እንደሆነ ይናገራል፤ ‹‹የተዘረጉ ክንፎቹ ይሸፍናሉ››
# አማኑኤል
ተርጓሚዎቹ፣ ‹‹አማኑኤል›› የሚለው ስም፣ ‹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር› ማለት ነው የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ያስፈልጋቸው ይሆናል፡፡ 7፥14 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡