# አጠቃላይ መረጃ ጌታ የአሦር ሰራዊት እንደ ወንዝ እየጐረፈ ወደ ይሁዳ እንደሚመጣ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ # ወንዙ እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል የአሦር ሰራዊት እንደ ውሃ ጐርፍ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከፍ እያለ ሄዶ እስከ ዐንገታችሁ እንደሚደርስ ወንዝ እጅግ ብዙ ወታደሮች ይመጣሉ›› # ወንዙ ይህ የሚያመለክተው በአሦር ያለውን የኤፍራጥስ ወንዝ ነው፡፡ ከቤታቸው ተነሥተው በኤፍራጥስ ወንዝ በኩል የሚመጡት የአሦር ወታደሮችም ምሳሌ ነው፡፡ (ኢሳይያስ 8፥7) # የተዘረጉ ክንፎቹ ይሞላሉ ይህም ማለት፣ 1) በምሳሌው እንዳየነው፣ ‹‹ወንዝ›› ወደ ደረቁ ምድር ‹‹ይወርዳል፣ ‹‹በክንፎቹም›› ይሸፍናል፡፡ ወይም 2) አሁን ኢሳይያስ ምሳሌውን በመለወጥ ያህዌ ምድሩን እንደሚጋርድ ወፍ እንደሆነ ይናገራል፤ ‹‹የተዘረጉ ክንፎቹ ይሸፍናሉ›› # አማኑኤል ተርጓሚዎቹ፣ ‹‹አማኑኤል›› የሚለው ስም፣ ‹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር› ማለት ነው የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ያስፈልጋቸው ይሆናል፡፡ 7፥14 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡