am_tn/isa/08/08.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ጌታ የአሦር ሰራዊት እንደ ወንዝ እየጐረፈ ወደ ይሁዳ እንደሚመጣ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ወንዙ እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል

የአሦር ሰራዊት እንደ ውሃ ጐርፍ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከፍ እያለ ሄዶ እስከ ዐንገታችሁ እንደሚደርስ ወንዝ እጅግ ብዙ ወታደሮች ይመጣሉ››

ወንዙ

ይህ የሚያመለክተው በአሦር ያለውን የኤፍራጥስ ወንዝ ነው፡፡ ከቤታቸው ተነሥተው በኤፍራጥስ ወንዝ በኩል የሚመጡት የአሦር ወታደሮችም ምሳሌ ነው፡፡ (ኢሳይያስ 8፥7)

የተዘረጉ ክንፎቹ ይሞላሉ

ይህም ማለት፣ 1) በምሳሌው እንዳየነው፣ ‹‹ወንዝ›› ወደ ደረቁ ምድር ‹‹ይወርዳል፣ ‹‹በክንፎቹም›› ይሸፍናል፡፡ ወይም 2) አሁን ኢሳይያስ ምሳሌውን በመለወጥ ያህዌ ምድሩን እንደሚጋርድ ወፍ እንደሆነ ይናገራል፤ ‹‹የተዘረጉ ክንፎቹ ይሸፍናሉ››

አማኑኤል

ተርጓሚዎቹ፣ ‹‹አማኑኤል›› የሚለው ስም፣ ‹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር› ማለት ነው የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ያስፈልጋቸው ይሆናል፡፡ 7፥14 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡