am_tn/ezk/39/25.md

28 lines
2.2 KiB
Markdown

# አያያዥ ሀሳብ፡
ያህዌ ለእስራኤል ስለሚሆነው ለሕዝቅኤል መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡
# የያዕቆብን እድል አድሳለሁ/ምርኮ እመልሳለሁ
"እድል ማደስ" የሚለውን በሕዝቅኤል 16፡53 ላይ ባለው መሰረት ይተርጉሙት፡፡ ሆኖም አንዳንድ ዘመናዊ ቅጂዎች የዕብራይስጡን አገላለጽ እዚህ ስፍራ "ያዕቆብን ከምርኮ እመልሳለሁ" ብለው ይተረጉሙታል፡፡
# የእስራኤል ቤት
"ቤት" የሚለው በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች፣ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ለሆኑ እስራኤላውያን ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
# ለቅዱስ ስሜ በቅናት እነሳለሁ
"እንደሚያከብሩኝ አረጋግጣለሁ"
# ሀፍረታቸውን እና ክህደታቸውን ሁሉ ይሸከማሉ
የትርጉም ባለሙያዎች በዚህ ሀረግ ትርጉም አይስማሙም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "በሀፍረት እና በክህደታቸው ሁሉ ይጸጸታሉ" ወይም 2) "ሀፍረታቸውን እና ክህደታቸውን ሁሉ ይረሳሉ"
# ክህደታቸው
"ታማኝ አለመሆናቸው"
# በብዙ አገራት እይታ ቅዱስ መሆኔን አሳያለሁ
እዚህ ስፍራ "እይታ" የሚለው ለመረዳት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ብዙ አገራት ለእስራኤል ቤት ከማደርገው የተነሳ እኔ ቅዱስ መሆኔን ይረዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)