am_tn/ezk/39/25.md

2.2 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለእስራኤል ስለሚሆነው ለሕዝቅኤል መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

የያዕቆብን እድል አድሳለሁ/ምርኮ እመልሳለሁ

"እድል ማደስ" የሚለውን በሕዝቅኤል 16፡53 ላይ ባለው መሰረት ይተርጉሙት፡፡ ሆኖም አንዳንድ ዘመናዊ ቅጂዎች የዕብራይስጡን አገላለጽ እዚህ ስፍራ "ያዕቆብን ከምርኮ እመልሳለሁ" ብለው ይተረጉሙታል፡፡

የእስራኤል ቤት

"ቤት" የሚለው በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች፣ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ለሆኑ እስራኤላውያን ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ለቅዱስ ስሜ በቅናት እነሳለሁ

"እንደሚያከብሩኝ አረጋግጣለሁ"

ሀፍረታቸውን እና ክህደታቸውን ሁሉ ይሸከማሉ

የትርጉም ባለሙያዎች በዚህ ሀረግ ትርጉም አይስማሙም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "በሀፍረት እና በክህደታቸው ሁሉ ይጸጸታሉ" ወይም 2) "ሀፍረታቸውን እና ክህደታቸውን ሁሉ ይረሳሉ"

ክህደታቸው

"ታማኝ አለመሆናቸው"

በብዙ አገራት እይታ ቅዱስ መሆኔን አሳያለሁ

እዚህ ስፍራ "እይታ" የሚለው ለመረዳት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ብዙ አገራት ለእስራኤል ቤት ከማደርገው የተነሳ እኔ ቅዱስ መሆኔን ይረዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)