# አያያዥ ሀሳብ፡ ያህዌ ለእስራኤል ስለሚሆነው ለሕዝቅኤል መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ # የያዕቆብን እድል አድሳለሁ/ምርኮ እመልሳለሁ "እድል ማደስ" የሚለውን በሕዝቅኤል 16፡53 ላይ ባለው መሰረት ይተርጉሙት፡፡ ሆኖም አንዳንድ ዘመናዊ ቅጂዎች የዕብራይስጡን አገላለጽ እዚህ ስፍራ "ያዕቆብን ከምርኮ እመልሳለሁ" ብለው ይተረጉሙታል፡፡ # የእስራኤል ቤት "ቤት" የሚለው በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች፣ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ለሆኑ እስራኤላውያን ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) # ለቅዱስ ስሜ በቅናት እነሳለሁ "እንደሚያከብሩኝ አረጋግጣለሁ" # ሀፍረታቸውን እና ክህደታቸውን ሁሉ ይሸከማሉ የትርጉም ባለሙያዎች በዚህ ሀረግ ትርጉም አይስማሙም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "በሀፍረት እና በክህደታቸው ሁሉ ይጸጸታሉ" ወይም 2) "ሀፍረታቸውን እና ክህደታቸውን ሁሉ ይረሳሉ" # ክህደታቸው "ታማኝ አለመሆናቸው" # በብዙ አገራት እይታ ቅዱስ መሆኔን አሳያለሁ እዚህ ስፍራ "እይታ" የሚለው ለመረዳት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ብዙ አገራት ለእስራኤል ቤት ከማደርገው የተነሳ እኔ ቅዱስ መሆኔን ይረዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)