am_tn/exo/29/01.md

28 lines
1.2 KiB
Markdown

# • የምታደርግባቸው ነገር ይህ ነው
እግዚአብሔር የካህናት ልብስ ዝግጅትና አሰራር ላይ የሰጠውን መመሪያ ጨርሶ ወደ ካህናትን ወደ መቀደስ ሥርዓት ሲሻገር እናያለን።
# • የምታደርግባቸው ነገር ይህ ነው
ይህን የሚሰራው ሙሴ እንደ ሆነ ማመልከቱ ነው።
# • ትቀድሳቸው ዘንድ
አሮንና ልጆቹ ካህናት ሆነው በፊቴ ወይም እኔን እንዲያገለግሉኝ የምትለያቸው
# • እንዲያገለግሉኝ
በአንደኛ መደብ የተገለጸው እግዚአብሔር /ያህዌ/ ነው። በሌላ አገላለጽ፦ “እኔን እንዲያገለግሉ”
# • አንድ ወይፈን
ቀንበር ያልተቀመጠበት ወጣት በሬ ማለት ነው
# • ቂጣ እንጀራ፥ በዘይትም የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ
እርሾ ያልነካው በወይራ ዘይት የታሸ ወይም ወይራ ዘይት የመጨመረበት ቂጣ
# • በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ ከመልካም ስንዴ
ምርጥ የሆነ የስንዴ ዱቄት ወስደህ ስስ/ቀጭን/ ቂጣ ጋግረህ ዘይት ቀባው